የመኖሪያ ቤት ሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
የሐራጅ ሽያጭ ማስታወቂያ
የፍ/ባለመብት ወ/ሮ ፈትለወርቅ ግርማይ እና የፍ/ባለዕዳ አቶ ግርማይ ዘሚካኤል መካከል ስላለው የፍርድ አፈጻጸም ጉዳይ የፌዴራል የመጀመሪያ ፍ/ቤት በመ/ ቁጥር 101873 በ24/02//2009ዓ/ም እና በኮ/መ/ቁ/196306 በ6/05/2016ዓ/ም በ27/05/2016 ዓ/ም በዋለው ችሎት በሰጠው ትዕዛዝ መሠረት በን/ስ/ላ/ክ/ከተማ ወረዳ 01 ጀሞ የጋራ መኖሪያ ቤቶች B1258 የቤት ቁጥር ጀ1-258/14 በተጠሪ ስም የተመዘገበ የቤቱ ስፋት 80.44 ካ/ሜ የባንክ ዕዳ አለበት የሐራጅ መነሻ ዋጋ ብር 5,374,759 (አምስት ሚሊዮን ሶስት መቶ ሰባ አራት ሺህ ሰባት መቶ ሀምሳ ዘጠኝ ብር 48/100) ሆኖ የትራዛክሽን ታክስ ገዥ የሚከፍል መሆኑ ታውቆ ሚያዝያ 24 ቀን 2016 ዓ.ም. በሐራጅ ይሸጣል፡፡ የተጫራቾች ምዝገባ 5፡00 ሰዓት ተጀምሮ የቀረቡ ተጫራቾች ተመዝግበው እንደተጠናቀቀ ወዲያውኑ ጨረታው የሚካሄድ ይሆናል፡፡
የሐራጁ ሽያጭ የሚካሄደው በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም ዳይሬክቶሬት የጨረታ አዳራሽ ውስጥ ሲሆን፣ ንብረቱን ተጫርተው ለመግዛት የሚፈልጉ ተጫራቾች ከጨረታው ቀደም ብሎ ባሉት አራት የሥራ ቀናቶች ውስጥ ባለመብቱ ለማስጎብኘት በሚመርጧቸው ሶስት የስራ ቀናት በፌ/ፍ/ቤቶች ፍርድ አፈፃፀም ዳይሬክቶሬት ሐራጅ ክፍል ድረስ ከጠዋቱ በ3፡30 ብቻ በመገኘትና ባለመብቱ በሚያቀርበው ትራንስፖርት ንብረቱን ባለበት ቦታ ድረስ በመውሰድ ለመጐብኘት የሚችሉ ሲሆን እያንዳንዱ ተጫራች በሚጫረትበት ወቅት የንብረቱን መነሻ ግምት 1/4 ኛውን በንግድ ባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ ይኖርበታል፡፡ ከ1/4ኛ አስበልጦም ሆነ አሳንሶ የሚያመጣ ታው አጽናን የሆነው ግለሰብ አሸናፊ ተጫራች በጨረታው አይካፈልም፡፡ በጨረታው አሸናፊ የሆነው ግለሰብ የሆነበትን ገንዘብ በአጠቃላይ ጨረታውን ከአሸነፈበት ቀን ጀምሮ በፍ/አፈ/ዳ/ ስም C.PO በኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ብቻ አሰርቶ ሙሉ ገንዘቡን በ15 ቀናት ውስጥ ገቢ ማድረግ አለበት፡፡ የፍ/አፈ/ዳይሮክቶሬቱ ንብረቱን በህጋዊ መንገድ በሐራጅ ስለመሸጡ ለሚመለከተው አካል ማስረጃ ከመጻፍ ባለፈ ስም የማዛወር ግዴታ የሌለበት መሆኑን እንገልፃለን፡
በፌዴራል ፍርድ ቤቶች የፍርድ አፈጻጸም
ዳይሬክቶሬት