በኢፌ.ዴ.ሪ የግ/ድ/ሠ/ማ/ዋ/ አስተዳደር የጅማ ዲስትሪከት ጽ/ቤት ለ2016 ዓ.ም በተፈቀደ በጀት የደንብ ልብስ ግዥ መፈፀም ይፈልጋል
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
የደንብ ልብስ ግዥ የጨረታ ማስታወቂያ
በኢፌ.ዴ.ሪ የግ/ድ/ሠ/ማ/ዋ/ አስተዳደር የጅማ ዲስትሪከት ጽ/ቤት ለ2016 ዓ.ም በተፈቀደ በጀት ከዚህ በታች የተዘረዘረውን መስፈርት የሚያሟሉ በጨረታው እንድትሳተፉ ይጋብዛል፡፡
1. የዘመኑ የታደሰ ህጋዊ ንግድ ፈቃድ ያለው፤
2. የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር /TIN NO/ ያለው፤
3. የቫት ተመዝጋቢ ማስረጃ ያለው ፤
4. ተጫራቾች ጨረታው በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ 15 የሥራ ቀናት ውስጥ የማይመለስ ብር 50.00 /ሃምሳ ብር/ በመክፈል የጨረታ ሰነዱን ዘወትር በሥራ ሰዓት በአስተዳደር ጽ/ቤት ግዥ ክፍል መግዛት የምትችሉ መሆኑን፤
5. ተወዳዳሪዎች ለሚወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ 2% (ሁለት በመቶ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ የተረጋገጠ (CPO) ከጨረታ ሰነዱ ጋር ተያይዞ ማቅረብ አለባቸው፤
6. ማንኛውም ተጫራች የእቃውን ዋጋ በመግለጽ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ኦርጂናሉንና ኮፒውን በመ/ቤታችን በተዘጋጀው የጨረታ ዶክመንት ማስገቢያ ሳጥን የጨረታ ማስታወቂያ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ከወጣበት ቀን አንስቶ እስከ 16ኛው የሥራ ቀን ከጠዋቱ 4፡00 (አራት ሰዓት) ድረስ ለጨረታው በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፤ ሳጥኑም በዚሁ ሰዓት ታሽጎ በዚሁ ዕለት ከቀኑ በ9፡00 (ዘጠኝ ሰዓት) ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት የጨረታ ሳጥኑ ይከፈታል፡፡
7. የጨረታው አሸናፊዎች ያሸነፉባቸውን እቃዎች በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፤
8.የሚቀርቡት እቃዎች በጨረታ ሰነዱ በተጠቀሰው ደረጃና ጥራት መሠረት መሆን ይኖርበታል፤
9. መ/ቤቱ እቃዎቹን በጨረታ ሰነዱ ከተጠቀሰው መጠን 20% መቀስ ወይም የመጨመር መብት አለው፤
10.መ/ቤቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ ሙሉ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ፡– በስልክ ቁጥር 047-111-70-07 መጠየቅ ይቻላል
በኢ.ፌ.ዴ.ሪ. የግል ድርጅት ሠራተኞች ማህበራዊ ዋስትና
አስተዳደር የጅማ ዲስትሪክት ጽ/ቤት
ጅማ