በጉለሌ ከፍለ ከተማ የሰላም ጤና ጣቢያ ለ2016 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣ የመድሃኒት ሪኤጀንቶች ፣ ሜዲካል ሰፕላይስ ፣ ህትመቶች እና የተለያዩ የጥገና ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
የጨረታ ማስታወቂያ 002/2016
በጉለሌ ከፍለ ከተማ የሰላም ጤና ጣቢያ ለ2016 በጀት ዓመት የሚያገለግሉ የጽህፈት መሳሪያዎች ፣ የጽዳት ዕቃዎች እና የተለያዩ ዕቃዎች ፣ የደንብ ልብስ ፣ የመድሃኒት ሪኤጀንቶች ፣ ሜዲካል ሰፕላይስ ፣ ህትመቶች እና የተለያዩ የጥገና ስራዎችን በጨረታ አወዳድሮ ለመግዛትና ለማሰራት ይፈልጋል፡፡
በመሆኑም የእያንዳንዱን የጨረታ ዝርዝር የያዘ ሰነድ ዘወትር በስራ ሰዓት ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቢሮ ቁጥር 31 ከዚህ በታች በተዘረዘረው መሰረት የማይመለስ ብር በመክፈል ሰነዱን መግዛት ይችላሉ፡፡
- ለጽህፈት መሣሪያዎች ……………ብር 100.00
- ለጽዳት ዕቃዎች እና ለተለያዩ ዕቃዎች……………. ብር 100.00
- ለአልባሳት (የደንብ ልብስ)…………………ብር 100.00
- ለመድሃኒት እና ለሪኤጀንት፣ ለሜዲካል ሰፕላይስ………….ብር 100.00
- ለህትመቶች………………ብር 100.00
- ለተለያዩ የጥገና ስራዎች………..ብር 50.00
ማሳሰቢያ፤
1. ተጫራቾች የዘመኑን ግብር የከፈሉ መሆን ይኖርባቸዋል ፣
2. ተጫራቾች የታደሰ የንግድ ፈቃድ ኮፒ ማቅረብ አለባቸው ፤
3. ተጫራቾች በየዘርፉ የተወዳደሩበት ጠቅላላ ዋጋ ብር 50,000 (ሃምሳ ሺህ ብር) ከሆነ የቫት ተመዝጋቢ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
4. ተጫራቾች የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና በCPO ብቻ ማስያዝ አለባቸው
- ለጽህፈት መሣሪያ……………ብር 700.00
- ለጽዳት ዕቃዎችና ለተለያዩ ዕቃዎች…………..ብር 1,400.00
- አልባሳት (የደንብ ልብስ)……………..ብር 3,532.00
- ለህትመት…………..ብር 500.00
- ለመድሃኒት ፡ ለፊኤጀንት እና ለሜዲካል ሰፐላይስ…………..ብር 55,442.00
- ለተለያዩ የጥገና ስራዎች………………ብር 4.532.00
5. የጨረታ ማስከበሪያ ያልያስያዘ ተጫራች ከውድድሩ ውጪ ይሆናል፡፡
6. ተጫራቾች የሚወዳደሩበትን ዋጋ ከጤና ጣቢያው በገዙት የጨረታ ሰነድ ላይ በመሙላት ኦሪጅናልና ፎቶ ኮፒ ለየብቻ በማሸግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ መክተት ይኖርባቸዋል፡፡
7. ተጫራቾች የመጫረቻ ሰነዶች ላይ ቫትን ማካተት አለባቸው የድርጅቱን ህጋዊ ማህተም ያላደረገ ፤ ስርዝ ድልዝ ያደረገ አማራጭ ዋጋ ሳምፕል ያቀረበ ተጫራች ተቀባይነት አይኖረውም።
8. ተጫራቾች ለሚወዳድሩበት ዕቃ ናሙና ማቅረብ ይኖርባቸዋል።
9. ተጫራቾች ያሸነፉበትን ዕቃ ጤና ጣቢያው ንብረት ክፍል ድረስ በራሳቸው ትራንስፖርት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
10. ጨረታው ይህ ማስታወቂያ በወጣ 10ኛው ቀን 11፡00 ላይ ተዘግቶ በ11ኛው ቀን ከጠዋቱ 4፡00 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
11. ተጫራቾች በጨረታው መሳተፍ እና ሰነድ መግዛት የሚችሉት በተሰማሩበት ዘርፍ ብቻ ነው።
12. ጤና ጣቢያው እንደአስፈላጊነቱ የዕቃውን ብዛት 20% ጨምሮ ወይም ቀንሶ መግዛት ይችላል።
13. ጨረታው ከተዘጋ በኋላ የሚመጣ ማንኛውም የተጫራች ሰነድ ተቀባይነት የሌለው መሆኑን እንገልጻለን፡፡
14. ተጫራቾች በተለያየ ንግድ ዘርፍ የሚወዳደሩ ከሆነ በየሎቱ ለየብቻ CPO ማስያዝ እንዲሁም ሰነዱን በየሎቱ በማሸግ በተዘጋጀው ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
15. ጤና ጣቢያው የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አድራሻ፡– 1. ከእንቁላል ፋብሪካ በላይ በእንቢልታ ሆቴል አስፋልት ወደ ላይ በሚያስወጣው መንገድ ከጎማ አደባባይ ከፍ ብሎ ሲሆን ከጉለሌ ክ/ከተማ ወረዳ 09 አስተዳደር ጀርባ
2. ከጳውሎስ ሆስፒታል አለፍ ብሎ ከጉለሌ ንግድ ባንክ ወደ ወረዳ 09 በሚያስወጣው አስፋልት
3. ከእንቁላል ፋብሪካ ወደ ሩፋኤል በሚወስደው 4 መንታ መንገድ ወረድ ብሎ
4. ከአዲሱ ገበያ አዲስ በተሰራው ጉለሌ ክፍለ ከተማ ወደታች ወረድ ብሎ
ስልክ ቁጥር፡-011-2-593899
011-2-593900
በጉለሌ አዲስ ከተማ ጤና መምሪያ የሰላም ጤና ጣቢያ