የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard service) ፣ ለስካይላይት ሆቴል እና ለሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የሥጋ እና የዶሮ ምርቶችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሶስት (3) ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሥራት ይፈልጋል
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር: SSNT-T449
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ለበረራ መስተንግዶ (onboard service) ፣ ለስካይላይት ሆቴል እና ለሠራተኞች ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚውል የተለያዩ የሥጋ እና የዶሮ ምርቶችን ከሚያቀርቡ ድርጅቶች ጋር በኮንትራት ስምምነት ለሶስት (3) ዓመት በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለመሥራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ከዚህ በታች የተገለጹትን መስፈርቶች የሚያሟሉ ተጫራቾች በጨረታው ላይ መሳተፍ ይችላሉ።
በአገልግሎቱ ዘርፍ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ፤ ለ2016 ዓ.ም የታደሰ የንግድ ሥራ ፈቃድ እና የTN ምዝገባ ወረቀት ያለው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆነ ፣ አንድ (1) ዓመትና እና ከዛ በላይ የሠራ ተጫራች በጨረታው መሳተፍ ይችላል፡፡
1. ተጫራቾች የጨረታ ሰነዱን ይህ የጨረታ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት ተከታታይ የሥራ ቀናት በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ አንድ መቶ ብር (ብር 100.00) በሂሳብ ቁጥር 1000006958277(E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ጨረታ ቁጥር SSNT-ፐ449 በሚል ገቢ በማድረግና የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ ኮፒ (Deposit Slip Copy) ቅጂውን (scan copy) በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ ሰነዱን ማግኘት ይችላሉ፡፡
2. በጨረታው የሚካፈል ማንኛውም ተጫራች 200,000.00 ብር (ሁለት መቶ ሺህ ብር ብቻ) የጨረታ ማስከበሪያ በባንክ በተረጋገጠ ሲ.ፒ.ኦ (CPO) ወይም የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርበታል፡፡ ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡
3. ተጫራቾች በጨረታው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካልና ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሚያዝያ 22 ቀን 2016 ዓ.ም ከቀኑ 9፡00 ሰዓት ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት አዲስ አበባ ቦሌ በሚገኘው የኢትዮጵያ አየር መንገድ ዋና መሥሪያ ቤት በተመሳሳይ ቀን ከቀኑ 9:30 ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ ፡–
የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ
ቦሌ ዓለም አቀፍ አየር ማረፊያ ዋና መሥሪያ ቤት
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
ጠይሜ ተሰጋ
ስልክ ቁጥር፡ 011-517-8953
ኢ–ሜይል: TeymeT@ethiopianairlines.com
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::