ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ስር ለሚገኙ ለተለያዩ አካባቢዎች የመጸዳጃ ቤት እና የአጥር ግንባታ ስራ ለማሰረት ብቁ የሆኑ ተጫረቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
የጨረታ ማስታወቂያ
ኢትዮ ቴሌኮም በደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ስር ለሚገኙ ለተለያዩ አካባቢዎች ማስትም፡ በአረካ የቦታ መለያ ቁ፤ 181136 ፡በካምባ የቦታ መለያ ቁ 181217 እና በቦኖሻ የቦታ መለያ ቁ 181296 የመጸዳጃ ቤት እና የአጥር ግንባታ ስራ ለማሰረት ብቁ የሆኑ ተጫረቾችን በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ ለማሰራት ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ በጨረታው ለመሳተፍ ፍላጎት ያላቸውና በመስኩ ደረጃ ሰባት(7) እና ከዚያ በላይ ፍቃድ ያላቸው ድርጅቶች የጨረታ ሰነዱን ዘወትር ከሰኞ እስከ አርብ በስራ ሰዓት ከኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሶርሲንግ እና ሰፕላይ ቼይን ቢሮ ቁጥር 104 ማግኘት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ ማስታወቂያ ከተነገረበት ቀን ጀምሮ እስከ 03/08/2016 ዓ.ም ድረስ ክፍት ሆኖ ይቆያል፡፡ ማንኛውም ተጫራች እስከ 03/08/2016 ዓ.ም ከቀኑ 11፡00 ሰዓት ድረስ የጨረታ መወዳደሪያ ሰነዱን በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሶርሲንግ እና ሰፕላይ ቼይን ቢሮ ቁጥር 104 ማስገባት ይኖርበታል፡፡ ጨረታው ፍላጎቱ ያላቸው ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት በ04/08/2016 ዓ.ም ከጠዋቱ 4፡00 ሰዓት በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሶርሲንግ እና ሰፕላይ ቼይን ቢሮ ቁጥር 104 ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ በኢትዮ ቴሌኮም ድረ ገጽ www.ethiotelecom.et ላይ ወይም ከ23/07/2016 ዓ.ም ጀምሮ ባሉት ቀናት ውስጥ በአዲስ ዘመን ጋዜጣ ላይ የታተመውን ዝርዝር ማስታወቂያ መመልከት ይቻላል፡፡ በተጨማሪም በኢትዮ ቴሌኮም ደቡብ ደቡብ ምዕራብ ሪጅን ሶርሲንግ እና ሰፕላይ ቼይን ቢሮ ቁጥር 104 ዘወትር በስራ ቀንና ሰዓት በአካል በመገኘት መጠየቅ ይችላሉ፡፡
መስፈርቶች
ሀ) የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና ሲ.ፒ.ኦ ፡ለካምባ የቦታ መለያ ቁ፡ 181217፡ ብር 60,000(ስልሳ ሺህ ብር)፤ለአረካ የቦታ መለያ ቁ፡181136፡ ብር 60,0000 (ስልሳ ሺህ ብር) እና ለቦኖሻ የቦታ መለያ ቁ፡181296፡ ብር 50,0000(ሃምሳ ሺህ ብር) ማስያዝ የሚችል፤
ለ) የ2015 ዓ.ም ግብር የከፈለ እና አግባብነት ያለው የታደሰ (በ2016 የንግድ ስራ ፈቃድ ያለው
ሐ) የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT and TIN) የምስክር ወረቀት
መ) የጨረታ ሰነድ ላይ ለመፈረም የሚያስችል ህጋዊ የውክልና ወረቀት
ሠ) ተጫራቾች በስነ ምግባር ደንቦች የመገዛት ቃልኪዳን ሰነድ/ቅጽ መሙላት ወይም ማዘጋጀት
ረ) ተጫራቹ የማቋቋሚያ ሰነድ (Legal establishment document) (በሽሙር ለተመሠረቱ ድርጅቶች ብቻ
ሰ) የዓመቱ የግብር ክፍያ ክሊራንስ ያለው
ሸ) በግንባታ ዘርፍ አንድ ዓመት የስራ ልምድ ያለው እና ከስራው ጋር ተጓዳኝ የሆኑ ሰነዶችን ማቅረብ የሚችል (ማለትም የክፍያ ሰርተፍኬት፡ የመልካም ስራ አፈጻጸም የምስክር ወረቀት እና ውል )
ቀ) ተጫራቾች ፋይናንሻል እና ቴክኒካል ዶክመንት ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም ሲ.ፒ.ኦ ለየብቻ በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ አድርገው በአንድ እናት ፖስታ በማድረግ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
ማስታወሻ ፡–
* ኢትዮ ቴሌኮም የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
አንድ ተጫራች ከአንድ ሳይት በላይ ሰነድ መግዛት አይችልም፡፡
ኢትዮ ቴሌኮም