በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት የአዲሱን ስርአተ ትምህርት መፅሐፍቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል
Bid closing date
ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በ15ኛው ቀን ልክ በ5፡15
Bid opening date
ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ በ15ኛው ቀን ልክ በ5:30
Published on
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
Posted
15 hours ago
Bid document price
200.00 ብር
Bid bond
20,000.00 ብር
Region
የጨረታ ማስታወቂያ
የጨረታ ቁጥር -042016
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት በ2016 በጀት ለት/ፅቤት ከ1ኛ-6ኛ ክፍል የተለያዩ የመማሪያ መፅሀፍት ከቨራቸዉ በከለር እና ዉስጡ በጥቁር የሆነ የአንዱን ገፅ ዋጋ በመግለፅ የአዲሱን ስርአተ ትምህርት መፅሐፍቶች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ማሳተም ይፈልጋል።
በዚህ መሰረት
- የ1ኛ ክፍል አማርኛ ፣ ሒሳብ ፣ አካባቢ ሳይንስ
- የ2ኛ ክፍል አማርኛ ፣ ሒሳብ ፣ አካባቢ ሳይንስ
- የ 3ኛ ክፍል አማርኛ ፣ ሒሳብ ፣ አካባቢ ሳይንስ
- የ 4ኛ ክፍል አማርኛ ፣ ሒሳብ ፣ አካባቢ ሳይንስ
- የ 5ኛ ክፍል አማርኛ ፣ ሒሳብ ፣ አካባቢ ሳይንስ
- የ 6ኛ ክፍል አማርኛ ፣ ሒሳብ ፣ አካባቢ ሳይንስ ፣ ግብረገብ
ከላይ በዝርዝር የተጠቀሱት ዕቃዎች በጨረታ ተወዳድሮ ለማቅረብ የሚፈልጉ ተወዳዳሪዎች
- በዘርፉ የታደሰ የንግድ ፈቃድ ያላቸው የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው ቲን ነምበር ያላቸውና የቫት ተዘመጋቢ የሆኑ፡፡
- ተጫራቾች ዝርዝር የጨረታውን ሰነድ ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ዉስጥ ዘወትር በስራ ሰዓት የማይመለስ ብር 200 ብቻ በመክፈል በማረቆ ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ ቤት ግዥና ንብረት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ቢሮ ቁጥር 5 በመቅረብ መግዛት ይችላሉ።
- ጨረታ ማስከበሪያ የሚሆን ገንዘብ ብር 20000(ሀያ ሺህ ብር) በጥሬ ገንዘብ ወይም በባንክ የተረጋገጠ ሲፒኦ /CPO/ በማረቆ ልዩ ወረዳ ፋ/ጽ/ቤት ስም በማሰራት ከጨረታው ሰነድ ጋር ማቅረብ አለባቸው፡፡
- ተሸናፊ ተጫራቶች ድርጅቶች ያስያዙትን ገንዘብ ወዲያው ይመለስላቸዋል፡፡ ተጫራቾች የዋጋ ማቅረቢያ ሰነድ ኦርጅናልና ኮፒውን ለየብቻ በሰም በታሸገ ኢንቫሎፕ በማድረግና ሙሉ አድራሻቸውን በመግለጽ ይህ ጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ በ15ኛው ቀን ከጠዋቱ 2፡30 እስከ 5፡00 ድረስ ለጨረታ በተዘጋጀው ጣጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
- ጨረታው በ15 ቀን ልክ 5፡15 ታሽጎ በዚህ ቀን ልክ 5:30 ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ነገር ግን ቀኑ የስራ ቀን ካልሆነ ወይም በአል ከሆነ በሚቀጥለው የስራ ቀን ይከፈታል::
- የጨረታ አሸናፊ የሆነ ተወዳዳሪ ድርጅቶች ያሸነፉትን ዕቃ ማ/ልዩ ወ/ፋ/ጽ/ቤት ግዥ ንብረት አስተዳደር ዋና የስራ ሂደት ድረስ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል፡፡
- መ/ቤቱ በጨረታ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ ስልክ 046 465 0044/45/46
ማሳሰቢያ፡- የሚታተሙ መጽሐፍቶችን ከልዩ ወረዳ ትምርህት ጽ/ቤት ስርዓተ ትምህርት ዳይሬክቶሬት ክፍል ማግኘት ይችላል፡፡
በማእከላዊ ኢትዮጵያ ክልል የማረቆ ልዩ ወረዳ ፋይናንስ ጽ/ቤት