መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉና ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
የጨረታ ማስታወቂያ
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር በቅጥር ግቢው ውስጥ የሚገኙትን ያገለገሉና ቁሳቁሶችን በጨረታ አወዳድሮ መሸጥ ይፈልጋል፡፡
- ቁሳቁሶቹም ወንበሮችና ተሽከርካሪ ወንበሮች፣ ጎማዎች፣
- የተለያየ መጠን ዓይነት ያላቸው እንጨት ነክ ዕቃዎች፣
- ጂፕሰም ቦርዶች ለኮርኒስ፣
- ያገለገሉ ሶፋዎች፣
- የተለያዩ የኤሌክትሮኒክስ ዕቃዎች፣
- የመኪና መለዋወጫዎች፣
- ከስብሰባ አዳራሽ የተፈቱ አዳዲስና አሮጌ የስብሰባ አዳራሽ ወንበሮች፣
- ለቀርከሃ አልጋ መወጠሪያ የተሠሩ ሸራዎች፣ የኮርኒስ መብራት ማቀፊያዎች (ፍሎረሰንት)፣
- የተለያዩ ቁርጥራጭ አሉሚኒየሞችና ጠፍጣፋ የፕላስቲክ ኮንዲዩቶች ናቸው፡፡
በመሆኑም መጫረት የሚፈልጉ ተጫራቾች አዲስ አበባ ከተማ፣ ለሚኩራ ክፍለ ከተማ ወረዳ 03፣ (በተለምዶ አያት ኮንዶሚኒየም፣ ከጠበል መድኃኔዓለም ቤተክርስትያን ፊት ለፊት) በሚገኘው በማዕከሉ ዋና መሥሪያ ቤት ቅጥር ግቢ ውስጥ ሲሆን ተጫራቾች ቁሳቁሶቹ በሚገኙበት ቦታ በመገኘት ከተመለከቱ በኋላ በማዕከሉ የጠቅላላ አገልግሎት ክፍል ድረስ በመምጣት ብር 200 በመከፈል የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
የጨረታ ሰነዱ በቁጥር 1፣ 2፣ እና 4 ቅጥር ግቢዎች ውስጥ ለሽያጭ የተዘጋጁትን ቁሳቁሶች ዝርዝር የያዘ ሲሆን እየተዘዋወሩ ከተመለከቱ በኋላ ዕቃዎቹን የሚገዙበትን ዋጋ በመሙላት በሰም በታሸገ ኤንቨሎፕ ካሸጉ በኋላ የጠቅላላ አገልግሎት ድረስ በመምጣት የጨረታውን ማስከበሪያ ቢድ ቦንድ ብር 90,000 (ዘጠና ሺህ ብር ብቻ) ከያዘ ሲፒኦ ጋር በተዘጋጀው የጨረታ ሣጥን ውስጥ ማስገባት ይችላሉ፡፡
ጨረታው ይህ የጨረታ ማስታወቂያ በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለተከታታይ 14 ቀናት ክፍት ሆኖ ቆይቶ በ15ኛው ቀን ከረፋዱ 4፡30 ሰዓት ተዘግቶ በዚሁ ዕለት በ5፡00 ሰዓት ተጫራቾችና ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡
ነገር ግን 15ኛው ቀን ዕሁድ ወይም ብሔራዊ በዓል ከሆነ በሚቀጥለው የሥራ ቀን ይሆናል፡፡ ድርጅቱ ጨረታውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለተጨማሪ ማብራሪያ በስልክ ቁጥር 8131 ወይም 0930-7964-13 ወይም 0975-26-41-59 ደውሎ መጠየቅ ይቻላል፡፡
መቄዶንያ የበጎ አድራጎት ማህበር