የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ሴክተር መ/ቤቶች በ2016 በጀት አመት በጋሞ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራዝ ልማት መምሪያ በጨንቻ ከተማ ሞዴል አንድ ማዕከል ለማስገንባት እና የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የወጋ መፅሔት ህትመት የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የተማሪ ካርድ ህትመት ለመግዛት ይፈልጋል
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
የጨረታ ማስታወቂያ
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ሴክተር መ/ቤቶች በ2016 በጀት አመት ሎት-1) በጋሞ ዞን ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራዝ ልማት መምሪያ በጨንቻ ከተማ ሞዴል አንድ ማዕከል ለማስገንባት እና ሎት-2) የጋሞ ዞን መንግስት ኮሚዩኒኬሽን ጉዳዮች መምሪያ የወጋ መፅሔት ህትመት ሎት 3) የጋሞ ዞን ትምህርት መምሪያ የተማሪ ካርድ ህትመት በአዲስ ዘመን ጋዜጣ አሳውጆ ለመግዛት ይፈልጋል።
በዚሁ መሠረት፦
1) ለሎት1) ደረጃቸው BC/GC 7 እና ከዚያ በላይ የሆኑ ተቋራጮች ሆነው የሕጋዊነት መረጃ ከሚመለከተው ኮንስትራክሽን ባለስልጣን በ2016 በጀት ዓመት የተመዘገቡ ወይም የብታት ማረጋገጫቸውን ያሳደሱ እና የ2015 በጀት አመት በኦዲተር የተረጋገጠ ግብር የከፈሉበትን ከሊራንስ ከገቢዎች ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ እንዲሁም በሁለቱም ሎት በዘርፉ የታደሰ ንግድ ሥራ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ ተመዝጋቢ የሆኑ፣ የግብር ከፋይነት መለያ ቁጥር (TIN NO) ያላቸው፣ የንግድ ምዝገባ ምስክር ወረቀት እና ሊአቅራቢነት በegp የተመዘገቡ፡፡
2) የሎት (1) ማንኛውም ተጫራቾች ከውድድሩ በፊት የሥራ ሳይቱን በራሱ ወጪ አይቶ ከጨንቻ ከተማ አስተዳደር ስራ ዕድል ፈጠራና ኢንተርፕራይዝ ልማት ጽ/ቤት ሳይቱን ስለማየቱ ማረጋገጫ ደብዳቤ በኦሪጅናል ቴክኒካል ሰነድ ውስጥ አስገብቶ ማቅረብ ይኖርበታል።
3) የሎት (1) ተጫራቾች አስፈላግውን የሣንባታ ዕቃና መሳሪያዎችን በራሳቸው ማቅረብ የምትችሉ፡–
4) የጨረታ ማስከበሪያ BID Security – ሎት-(1) 120,000(አንድ መቶ ሃያ ሺህ ብር) ለሎት(2 ና 3) 10,000(አስር ሺህ) ብር በባንክ በተረጋገጠ የክፍያ ማዘዣ (CPO) (በጥሬ ገንዘብ) ወይም በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ የባንከ ጋራንቲ ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
5) ተጫራቾች ሕጋዊ ፈቃዳቸውንና የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) የተመዘገቡበትን ሠርተፍኬት በማቅረብ የጨረታውን ዶክመንት ይህ ማስታወቂያ አየር ላይ ከዋለበት ቀን አንስቶ ለሎት1 እስከ 21 (ሃያ አንደኛው) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 300(ሦስት መቶ ብር) ለሎት(2ና3) እስከ 15(አስራ አምስተኛው) ተከታታይ ቀናት የማይመለስ ብር 100 (አንድ መቶ ብር) በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ የባንክ ሂሳብ ቁጥር 1000038613263 በማስገባት እና የባንክ አድቫይስ ይዘው ከጋሞ ዞን ገቢዎች መምሪያ ደረሰኝ በመቁረጥ ከዞኑ ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ቀርበው ደረሰኙን በማሳየት የጨረታ ሰነድ መውሰድ ይችላሉ፡፡
6) ተጫራቾች ለሎት (1) የፋይናንሻል ጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ አንድ ኦርጅናልና ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒው በተለያዬ ፖስታ ታሽጎ ኦርጅናልና ኮፒ ተብሎ እላዩ ላይ ተጽፎበት : በሶስቱም ፖስታዎች ላይ ስም ፣ አድራሻና የፕሮጀክቱ ስም በመጻፍ ሕጋዊ የሆነ ማህተም በማሳረፍና በመፈረም እንዲሁም– የህጋዊ ተክኒካል ሰነዶችን አንድ ኦርጂናል ሁለት ፎቶግራፊክ ኮፒ በተለያዬ ፖስታ ከላይ በተገለጸው በተመሳሳይ ሁኔታ ታሽጎ እና ሁሉንም ፖስታዎች በአንድ እናት ፖስታ እላዩ ላይ ማህተም ፡ አድራሻና ስም ጽፎ በመፈረም አሽጎ ለሎት(2ና3) የፋይናንሻል ጨረታ ሰነዱ ተሞልቶ እና የህጋዊ ተክኒካል ሰነዶችን በፖስታ አስገብቶ የጨረታውን አይነት ጽፎ እላዩ ላይ ማህተም አድራሻና ስም ጽፎ በመፈረም አሽጎ ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ለሎት(1) እስከ 22ኛው ተከታታይ ቀን እና ለሎት(2ና3) እስከ 16ኛው ተከታታይ ቀን 4፡00 ሰዓት ድረስ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ግዥና ን/አስ/ዳይሬክቶሬት ቢሮ ቁጥር 5 ለዚሁ በተዘጋጀው የጨረታ ሳጥን ውስጥ ዘውትር በስራ ሰዓት ማስገባት ይኖርባቸዋል፡፡
7) ጨረታው ሎት (1) በ22ኛው (ሃያ ሁለተኛው) ሎት (2ና3) በ16ኛው(አስራ ስድተኛው) ቀን በ4፡00 ሰዓት ታሽጎ ልክ በ4፡30 ሰዓት ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል፡፡ ዕለቱ የስራ ቀን ካልሆነ በቀጣዩ የስራ ቀን በተመሳሳይ ቦታና ሰዓት ታሽጎ ይከፈታል፡፡
የተጫራቾች አለመገኘት ጨረታውን ከመከፈት አያስተጓጉልም፡፡
ማሳሰቢያ፡– መ/ቤቱ የተሻለ ዘዴ ካገኘ ጨረታውን በሙሉም ሆነ በከፍል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡
ለበለጠ መረጃ በጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ስልክ ቁ 046-881-3338 ይደውሉ፡፡
የጋሞ ዞን ፋይናንስ መምሪያ ለዞኑ ሴክተር መ/ቤቶች