የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
የሸቀጥ ግዥ ጨረታ (ቁጥር ዐ04/2016)
ድርጅታችን የኢትዮጵያ የደረጃዎች ኤጀንሲ ያወጣውን የጥራት መስፈርት የሚያሟሉ እና ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን ሸቀጦች በግልፅ ጨረታ አወዳድሮ መግዛት ይፈልጋል::
- አንደኛ ደረጃ የዳቦ ዱቄት CES 1052:2021
- ፓስታ CES 1055:2022
- የተለያየ መጠን ያላቸው የፍራሽ ምርቶች
- የተለያየ መጠን ያላቸው የጎማ ምርቶች
- የተለያየ መጠን ያላቸው ከጥጥ የተሠረተ የአንሶላ ምርቶች
- የተለያየ መጠን ያላቸው የብርድ ልብስ ምርቶች
- መደበኛ የቤት ክዳን ቆርቆሮ CES 40፡2021
- የልብስ ሳሙና CES 42፡2021
- በሀገር ውስጥ የተመረተ ፈሳሽ የሱፍ ዘይት CES17: and labeling CES 73
- ደብተር
በጨረታው መካፈል የሚፈልጉ ተጫራቾች፡
1. ደብተር ጎማ እና መደበኛ የቤት ክዳን ቆርቆሮ አምራች ወይም አስመጭና አከፋፋይ እንዲሁም ለተቀሩት ምርቶች አምራች ብቻ መሆን ይጠበቅባቸዋል::
2. በዘርፉ የታደሰ የንግድ ስራ ፍቃድ፣የንግድ ማዝገባ ፈቃድ ተጨማሪ ዕሴት ታክስ የተመዘገቡ፤ የግብር ከፋይነት
ምዝገባ ሠርቴፍኬት እና የግብር ክሊራንስ ያላቸው መሆን ይገባቸዋል::
3. ለጨረታ የተዘጋጀውን ዝርዝር የጨረታ ሠነድ የማይመለስ ብር 200.00 (ሁለት መቶ ብር) በመክፈል ቢስ መብራት
ከሚገኘው የድርጅቱ ዋና መስርያ ቤት የኢዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት ቢሮ በመቅረብ መግዛት ይችላሉ::
4. የጨረታ ማስከበሪያ ዋስትና (ለእያንዳንዱ ምርት በጨረታ ሰነዱ ላይ በተጠቀሰው መሰረት) ለብቻው በታሸገ ኤንቬሎፕ በማድረግ ማቅረብ ይጠበቅባቸዋል::
5. የጨረታ መወዳደሪያ ዋጋቸውን(financial)ና ከላይ ከተጠቀሱት ህጋዊ ሠነዶች(technical) በተለያየ የታሸገ ኤንቨሎፕ አንድ ኦሪጅናል እንዲሁም አንድ ኮፒ በማድረግ እስከ መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡00 ሠዓት ድረስ ማቅረብ ይችላሉ::
6. ጨረታው በተመሳሳይ መጋቢት 27 ቀን 2016 ዓ.ም ከረፋዱ 4፡10 ሠዓት ላይ ተጫራቾች ወይም ህጋዊ ወኪሎቻቸው በተገኙበት ይከፈታል:: ከጨረታ መዝጊያ ሰዓቱ በኋላ የሚቀርብ ሰነድ ተቀባይነት የለውም
ድርጅቱ የተሻለ አማራጭ ካገኘ ጨረታውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው::
የኢትዮዽያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
የኢንዱስትሪ ውጤቶች ግዥ ዳይሬክቶሬት
ስልክ ቁጥር 0113692436
Company Info
Ethiopian Industrial Inputs Development Enterprise
የኢትዮጵያ ኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት
Address | ቃሊቲ ጉምሩክ ፊት ለፊት የኢትዮጵያ የኢንዱስትሪ ግብዓቶች ልማት ድርጅት ማዕከላዊ ዲስትሪክት ቃሊቲ ቅርንጫፍ ጽ/ቤት |
---|