የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተለያዩ የህትመት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በጨረታ አወዳድሮ ለሶስት ዓመት በኮንትራት በስምምነት ማሰራት ይፈልጋል



Bid closing date
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00

Bid opening date
ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 9:30

Published on

አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)

Posted

Bid document price
100/አንድ መቶ ብር/

Bid bond
50,000.00 /ሃምሳ ሺህ ብር/

Region


የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏
የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ቁጥር: SSNT- T447

የኢትዮጵያ አየር መንገድ የተለያዩ የህትመት አገልግሎት ሰጪ ድርጅቶችን በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ ለሶስት ዓመት በኮንትራት በስምምነት ማሰራት ይፈልጋል፡፡

ስለሆነም ለስራው ብቁ የሆኑ ተጫራቾች ፣ በህትመት አገልግሎት ለ3 ዓመት እና ከዛ በላይ የሰሩ የዘመኑን የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፣ የተጨማሪ እሴት ታክስ (VAT) ተመዝጋቢ የሆኑ ፣ የዘመኑን ግብር የከፈሉ፣ በመንግስት ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ዎች ለመሳተፍ ፈቃድ ያላቸው እና ከግብር እዳ ነጻ ስለመሆናቸው ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡

ተጫራቾች ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ው በጋዜጣ ከወጣበት ቀን ጀምሮ እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ባሉት 30 ተከታታይ ቀናት የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱን ለመውሰድ በአቅራቢያቸው ከሚገኝ የኢትዮጵያ ንግድ ባንክ ቅርንጫፍ የማይመለስ 100.00 ብር አንድ መቶ ብር/ በመክፈል በሂሳብ ቁጥር 1000006958277 (E-99) ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ቁጥር (SSNT- T447) በሚል ገቢ ማድረግ ይኖርባቸዋል፡፡ ተጫራቾች የከፈሉበትን የገቢ ደረሰኝ (Deposit Slip) ስካን በማድረግ ከታች በተጠቀሰው የኢሜይል አድራሻ በመላክ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱን በኢሜል ማግኘት ይችላሉ፡፡

ተጫራቾች ለጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ብር 50,000:00 /ሃምሳ ሺህ ብር/ በባንክ የተረጋገጠ ቼክ /ሲፒኦ/ ወይም ለ90 ተከታታይ ቀናት የሚቆይ ምንም አይነት ቅድመ ሁኔታ የሌለው የባንክ ዋስትና ማቅረብ ይኖርባቸዋል:: ከማንኛውም ኢንሹራንስ የሚቀርብ ዋስትና ተቀባይነት አይኖረውም፡፡ አሸናፊው ከተለየ በኋላ በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ው ለተሸነፉት ተጫራቾች ያስያዙት የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ ወዲያውኑ ተመላሽ ይሆናል:: ተጫራቾች በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ው ደንብ መሠረት የመጫረቻ ሠነዳቸውን (ቴክኒካል፣ ፋይናንሻል) ዋናውን እና ኮፒውን እንዲሁም የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያውን በታሸገ ኤንቨሎፕ ለኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ክፍል እስከ ሚያዝያ 18 ቀን 2016 ዓ.ም. ከቀኑ 9:00 ሰዓት‍‌‌‌‍‍‍‍‌‌‍‍‍‌‍‌‍ ድረስ ማቅረብ አለባቸው፡፡ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ው ተጫራቾች ወይም ወኪሎቻቸው በተገኙበት በተመሳሳይ ቀን 9፡30 ሰዓት የኢትዮጵያ አየር መንገድ ግሩፕ ዋና መሥሪያ ቤት በሚገኘው የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ መክፈቻ አዳራሽ ውስጥ ይከፈታል፡፡

ተጨማሪ ማብራሪያ፦ የኢትዮጵያ አየር መንገድ ቦሌ አለም አቀፍ አየር ማረፊያ
ስትራቴጂክ ሶርሲንግ ነን ቴክኒካል ክፍል
በስልክ ቁጥር 011 517 8025 በመደወል መጠየቅ ይቻላል:: ኢሜል: HELENN@ethiopianairlines.com 
አየር መንገዱ የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ውን በከፊልም ሆነ በሙሉ የመሠረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

Company Info