በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ ይፈልጋል
Bid closing date
ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ
Bid opening date
ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት በ16ኛው ቀን በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተጠቀሰው ቦታ ቀንና ሰዓት
Published on
አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)
Posted
12 hours ago
Bid document price
Bid bond
Region
የአፈር ማዳበሪያ ለማጓጓዝ የወጣ ግልጽ
የጨረታ ማስታወቂያ
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ የማዕከላዊ ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ ለ2016/2017 የምርት ዘመን አገልግሎት የሚውል ኤንፒኤስ ቦሮን ፤ እና ዩሪያ የአፈር ማዳበሪያ ከሰላም ዩኒዬን ማእከላዊ መጋዘን ወደ መ/ ማህበራት በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለማጓጓዝ ይፈልጋል።
ስለዚህ በሥራው ላይ ለመሳተፍ የምትፈልጉ የደረቅ ጭነት ማመላለሻ ባለንብረቶች ማኅበር (የግል ባለንብረቶች) በአዲስ አደረጃጀት የብቃት ማረጋገጫ ከሚመለከተው አካል ማቅረብ የምትችሉ አጓጓዦች የማጓጓዣ ታሪፋችሁን በማራገፊያ ጣቢያዎች ዝርዝር መሠረት በታሸገ ፖስታ በማቅረብ በጨረታ መሳተፍ ትችላላችሁ።
በመሆኑም በጨረታው መወዳደር የምትፈልጉ፡–
- በዘርፉ የታደሰ ህጋዊ የንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
- የግብር ከፋይ ምዝገባ ሰርተፊኬት ያላቸው፡፡
- የተጨማሪ እሴት ታክስ የምዝገባ የምስክር ወረቀት ያላቸው፡፡
- ከዚህ በፊት በአፈር ማዳበሪያ የማጓጓዝ ተግባር ላይ መልካም አፈፈፃፀም ያላቸው
- ተጫራቾች ከ70 ኩ/ል በላይ የሚጭኑ ተሽከርካሪዎችን የሚያቀርቡ ከሆነ ከፌዴራል ትራንስፖርት ባለስልጣን ተመዝግበው የተደራጁ ሆነው በዘመኑ የታደሰ የብቃት ማረጋገጫ ማቅረብ የሚችሉ መሆን አለባቸው፡፡ ተጫራቾች ይህ ማስታወቂያ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 15 ተከታታይ ቀናት ውስጥ ማዕከላዊ ጎን/ዞን/ገን/ኢት/ብ/መምሪያ ቢሮ ቁጥር 22 በመምጣት የተሟላ የጨረታውን ዝርዝር ማስታወቂያና ሙሉ የጨረታ ሰነዱን መግዛት ትችላላችሁ ጨረታው ጋዜጣው በወጣ በ16ኛው ቀን በጨረታ ማስታወቂያው ላይ በተጠቀሰው ቦታ ቀንና ሰዓት ይከፈታል፡፡
ለበለጠ መረጃ፡–
ስልክ ቁጥር 0581110649
ፋክስ ቁጥር 0581110965 መደወልና ፋክስ ማድረግ ትችላላችሁ፡፡
በአማራ ብሔራዊ ክልላዊ መንግሥት የግብርና ቢሮ የማዕከላዊ
ጎንደር ዞን ግብርና መምሪያ