በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ለ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ የተለያዩ እቃዎች በግልጽ ጨረታ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋልBid closing date
ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ3፡00 ሰዓት

Bid opening date
ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ቆይቶ በ11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ3፡30 ሰዓት

Published on

አዲስ ዘመን
(Mar 28, 2024)

Posted

Bid document price
200.00 (ሁለት መቶ ብር)

Bid bond
ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ)

Region


የግልጽ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏

በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ለ2016 ዓ.ም በጀት ዓመት አገልግሎት የሚውሉ ከዚህ በታች የተዘረዘሩትን እቃዎች በግልጽ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ አወዳድሮ ለመግዛት ይፈልጋል፡፡

 1. የደንብ ልብስ
 2.  ቋሚ የቢሮ እቃ
 3.  አላቂ የቢሮ እቃ
 4.  የፅዳት እቃ
 5. ቋሚ የህክምና መሳሪያዎች
 6.  የላብራቶሪ ኤጀንት
 7.  መድሐኒት
 8.  ህትመት
 9.  የቢሮ እቃዎች ጥገና
 10.  የአካባቢ አያያዝ እቅድ ዝግጅት ባለሙያ
 11.  ልዩ ልዩ እቃዎች
 12.  የሰራተኛ መመገቢያ ካፍቴሪያ አገልግሎት የሚሰጥ

በዚህ መሰረት በጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ው መሳተፍ የሚፈልጉ፤

 1. በተሰማሩበት ዘርፍ በዘመኑ የታደሰ ንግድ ፈቃድ ያላቸው፡፡
 2.  የግብር ከፋይ መለያ ቁጥር ያላቸው፡፡
 3.  የዘመኑን ግብር አጠናቀው የከፈሉ ለዚህም ማስረጃ ማቅረብ የሚችሉ፣
 4. የተጨማሪ እሴት ታክስ ከፋይነት የተመዘገቡ፡፡
 5. በአቅራቢዎች ዝርዝር ውስጥ የተመዘገቡ መሆን ይኖርባቸዋል፡፡
 6.  ለጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ማስከበሪያ የሚውል በባንክ በተረጋገጠ CPO ለእያንዳንዱ ለሚወዳደሩበት ብር 2,000.00 (ሁለት ሺህ) ማስያዝ ይኖርባቸዋል፡፡
 7.  ለጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ሰነድ 200.00 (ሁለት መቶ ብር) የማይመለስ በመክፈል ይህ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ከወጣበት ቀን ጀምሮ ባሉት 10 ተከታታይ የስራ ቀናት ከ2፡30 እስከ 11፡00 ሰዓት‍‌‌‌‍‍‍‍‌‌‍‍‍‌‍‌‍ ድረስ ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ቢሮ ቁጥር 406 በግንባር በመቅረብ መግዛት ይቻላል፡፡
 8.  ተጫራቾች የሚጫረቱበትን እቃ ናሙና ለሚያስፈልጋቸው ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ው ከመከፈቱ በፊት ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡
 9. የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱ 2 ኮፒና ኦሪጅናል በመለየት በተለያዩ ፓስታ አሽገው ሲመጡ CPO ደግሞ የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ው ኮፒ ባለበት ፓስታ ውስጥ በማስገባት አሽገው ማቅረብ ይኖርባቸዋል፡፡ 
 10. ተጫራቾች የሚጫረቱበትን ዋጋ ዝርዝር ሰነዱ ላይ ባለው የዋጋ ማቅረቢያ በግልጽ ሞልተው ይህ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ከወጣበት እለት ጀምሮ እስከ 11ኛው የስራ ቀን ከቀኑ በ3፡00 ሰዓት ድረስ ለዚሁ በተዘጋጀ ሳጥን ውስጥ ማስገባት ይኖርባቸዋል፡
 11. . የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ሳጥኑ ማስታወቂያ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ው ከወጣበት በ11ኛው ቀን በጤና ጣቢያው ቅጥር ግቢ አዳራሽ ውስጥ በ3፡30 ሰዓት ይከፈታል፡፡ ቀኑ በአል ላይ ከዋለ በሚቀጥለው የስራ ቀን በተጠቀሰው ሰዓት ይከፈታል፡፡
 12.  የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ ሰነዱ ላይ ስርዝ ድልዝ ካለ ለውድድር አይቀርብም፡፡
 13. የጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ አሸናፊው ያሸነፈበትን እቃ የጠቅላላ ዋጋ 10% ዋስትና በባንክ በተረጋገጠ CPO ማስያዝ አለበት፡፡
 14. ጤና ጣቢያው የተሻለ መንገድ ካገኘ ጨረታ‏‎‎‎‏‏‏‏‎‎‏‏‏‎‏‎‏ውን ሙሉ በሙሉ ወይም በከፊል የመሰረዝ መብቱ የተጠበቀ ነው፡፡

የአካባቢ አያያዝ እቅድ ዝግጅት ባለሙያ ላይ የሚወዳደሩ ተጫራቾች ይህንን መስፈርት ማሟላት ይኖርባቸዋል፡፡

 1. የብቃት ማረጋገጫ የምስክር ወረቀት መታሰር አለበት (ከአካባቢ ጥበቃ ባለስልጣን የተሰጠ)
 2.  ዝርዝር የባለሙያዎች መረጃ ማደራጀት (የትምህርት ዝግጅት, ስልክ ቁጥር)
 3.  TOR (Term of Reference)
 4.  Public Consultation (ውይይቶች, ቃለ መጠይቆች ወዘተ…)
 5.  EMP Include Map and Diagram
 6.  ካርታ የአከራይ ተከራይ ውል የውል ስምምነት የንግድ ፈቃድ መያያዝ አለበት አድራሻ፡- በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 04 ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ጎተራ ኮንዶሚኒየም ሙሉ ወንጌል ቸርች አጠገብ

ስልክ ቁጥር፡-011-8-68 18 24/20
በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ

Company Info

Felege Hiwot Health Post

ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ

Address በቂርቆስ ክፍለ ከተማ ጤና ጽ/ቤት የወረዳ 04 ፈለገ ህይወት ጤና ጣቢያ ጎተራ ኮንደሚኒየም ሙሉ ወንጌል ቸርች አጠገብ